
በኢትዮጵያ በርካታ የሰብአዊ ስራዎችን በመስራት የሚታወቁት የሰዎች ለሰዎች ድርጅት መስራቹ ካር ሄንዝ በም ለረጅም ጊዜ በህመም ሲሰቃዩ ቆይተው ነው ግንቦት 21/2006 ቀን በጀርመን ሳልበርግ ህይወታቸው ያለፈው፡፡
በህመም ምክንያት የድርጅታቸውን ሀላፊነት አሳልፈው ሰጥተው የነበሩ እኝህ በጎ አድራጊ በብዙ ኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥም በሰሩት ስራ ሲዘከሩ ይኖራሉ፡፡
ካርል በቅርብ ለረጅም ጊዜ የህመማቸው አይነት ሳይታወቅ ቆይቶ አልዛይመር መሆኑ ባለፈው አመት እንደታወቀ ተገልጿል፡፡
በ1928 በጀርምን የተወለዱት ኦስትሪያዊ ሚስተር ካርል በፊልሙ አለምም "ንጉሰ ነገስት ፍራዝ ጆሴፍ " በተሰኘው ተከታታይ ፊልም በ1950ዎቹ የታወቁበት ስራቸው ነበር፡፡
ትናንት በህክምና እየተረዱ ባለበት ሆስፒታል ህይወታቸው ማለፉን የጀርመኑ ዶቼ ቨሌ የእንግሊዝኛው ክፍል ዘግቧል፡፡
ካርል በኢትዮጵያ ልማት ሙሉ ጊዘያቸውን ከመስጠታቸውም የተነሳ ኢትዮጵያዊት ባለቤታቸው ጋር ትዳር መስርተው የኃላ ኃላ ድርጅቱን ሀላፊነት ሙሉ ለሙሉ ለባለቤታቸው አስተላልፈው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
ሚስተር ካርል ሄንዝ በም በኢትዮጵያ ላበረከቱት ዘርፈ ብዙ የልማት ስራ መንግስት የክብር ዜግነት ስጥቷቸዋል፡፡ የመታሰቢያ ሀውልት አዲስ አበባ ላይ አቁሞላቸዋል፡፡
የጅማ ዩኒቨርሲቲም የክብር ዶክትሬት ሰጥቷቸዋል፡፡
0 comments:
Post a Comment