ኢትዮጵያና ቻይና በአዲስ አበባ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ዞን ሊያቋቁሙ ነው።
የቻይናው ዜዥያንግ ዢንዳ ፍላክስ የተባለው ኩባንያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ የኢንዱስትሪ ዞኑን ያቋቁማል።
ኩባንያውና የኢፌዴሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፕሮክቱን ለመጀመር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ለኢንዱስትሪ ዞኑ ግንባታ የሚያስፈልገው የመሬት መጠን ዝግጁ ሲሆንም፥ ሚኒስቴሩ የመጨረሻውን ይፋዊ ስምምነት በሀምሌ ወር ከኩባንያው ጋር ይፈራረማል ተብሏል።
ሚኒስቴሩ በሁለት ሳምንታት ውስጥ መሬትን በተመለከተ ለኩባንያው ዝርዝር መረጃዎችን እንደሚያቀርብ አስታውቋል።
የቻይና ኪንግደም ሆልዲንግ ኩባንያ አካል የሆነው ዜዥያን ግዢንዳ ፍላክስ በሶፋ መጋረጃና ጨርቆች እንዲሁም በአልጋ ልብስ ምርቶች ይታወቃል።
እስከ ሚቀጥለው ዓመት ሰኔ ወር ድረስም ኩባንያው የኢንዱስትሪ ዞኑን ግንባታ የመጀመሪያ ምእራፍ ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል።
50 ኢትዮጵያውያንባለሙያዎችንወደቻይና ወስዶማሰልጠንምበስምምነቱውስጥተካቷል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 250 የሚሆኑ የጨርቃ ጨርቅና ቆዳ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙ ሲሆን 11 የሚሆኑ ግዙፍ   ኩባንያዎችም በዚህ ዘርፍ ተሰማርተው ይገኛሉ ሲል ፋና ቢ ሲ ዘግቧል።

0 comments:

Post a Comment

 
Top