አጥሬን ነቀላችሁ በሚል በተነሳ ፀብ ባልና ሚስቶቱን በጥይት በአስቃቂ ሁኔታ የገደለው ምርመራው ተጠናቆ ክስ እንደተመሰረተበት የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ተከሳሹ አስቀድሞ ሰው ለመግደል አስቦ በመዘጋጀት በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ መካኒሳ ጉሊት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አካባቢ ሲሆን በድንበር ግጭት ምክንያት የተፈጠረውን አለመግባባትና በቀበሌና በማህበራዊ ፍርድ ቤት በክርክር ላይ ያለውን ጉዳይ ቂም በመያዝ በህገ-ወጥ መንገድ በቤት ውስጥ የነበረውን ክላሽ እና 3 ሙሉ ካርታ ጥይት በመያ ሟቾችን ባልና ሚስት የሆኑትን 1ኛ አቶ ዳንኤል ነጋሽን 20 የክላሽ ጥይቶችን ተኩሶ ከገደለው በኋላ ጥይት ሲያልቅበት ሌላ ካርታ በመቀየር 2ኛዋን ሟች ወ/ሮ አምሳለ ሸሽታ ከተደበቀችበት ከመኖሪያ ቤቷ በመሄድ በመኝቷ ክፍሏ ውስጥ በ11 ጥይቶች ደብድቦ በመግደሉና በፈፀመው በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ተከሷል ሲሉ የወንጀሉ መርማሪ የሆኑት ዋ/ሳ ግሩም ታረቀኝ ተናግረዋል፡፡
በተከሳሹ ላይ 2ኛ ክስ እንዲመሰረትበት ምክንያት የሆነው በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 03 ክልል የቤት ቁጥር 396 ከሆነው መኖሪያ ቤቱ መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ገደማ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲበርበር 1 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ 2ኛ የተፈታታ ማካሮቭ ሽጉጥ ከአንድ ካርታ የሽጉጥ ጥይት ጋር 3ኛ አንድ የጦር ሜዳ መነጽር 4ኛ ብዛቱ 46 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይቶች 5ኛ ሦስት ባዶ የክላሽ ካርታዎች ያለፈቃድ ቤቱ በመገኘታቸው ክስ ሊመሰረትበት ችሏል፡፡ ተጠርጣሪው ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ ሊያመልጥ ሲሞክር በአካባቢው ባሉ ሰዎችና በቦታው በፍጥነት በደረሱ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባሎች ተከቦ ሊያዝ እንደቻለ ተገልጿል፡፡ ተከሳሽ የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበረና በአካል ጉዳት ምክንያት በቦርድ የተሰናበተ ሲሆን መሳሪያውን ከየት እንዳመጣ ሲጠየቅ ከሰራዊቱ ይዞት እንዳልወጣ የተናገረ ቢሆንም ፖሊስ ባጣራው መሰረት ማንኛውም ከመከላከያ ሰራዊት አባል በጡረታ ሲገለል የጦር መሳሪያውን እንደሚያስረክብ ከተቋሙ
እንደተገለፃላቸው መርማሪው አስረድተዋል፡፡ ፖሊስም አስፈላጊውን የሰውና የሰነድ ማስረጃን
ካሰባሰበ በኋላ ለፌደራሉ ከፍተኛ ዐቃቢ ህግ የላከው ሲሆን አቃቢ ህግም ክስ እንደመሰረተበትና ተከሳሽም በማረሚያ ሆኖ ክሱን እየተከታተለ እንደሆነ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው መግደል ወንጀል ምርመራ የተገኘ ማስረጃ ያመለክታል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው መግደል ወንጀል
መርማሪ ሀላፊ የሆኑት ም/ሳጅን መንግስቱ ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት ማንኛውም አለመግባባቶች
በውይይት ካልተቻለም በፍትህ ተቋማት ሊፈቱ ሲገባ እንደዚህ አይነት ወንጀል መፈፀም አግባብ አለመሆኑን ገልፀው ሟቾችም ልጆች የነበራቸው በመሆኑ ልጆቹን ለከፍተኛ ጉዳት ተጋልጠዋል ብለዋል፡፡
Next
This is the most recent post.
Previous
Older Post

0 comments:

Post a Comment

 
Top