በድህነት ትታወቅ የነበረችው ኢትዮጵያ በሁለት አስርት አመታት ውስጥ በምግብ ራሷን መቻሏ የግንቦት 20 ቱርፋት መሆኑን ጠቅላይ ሚንስተር ሀይለማሪያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡
የግንቦት ሀያ 23ኛ አመት ክብረ በዓል ማጠቃላያ በአዲስ አበባ ስታዲዮም በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡
በበኣሉ ላይ የተገኙት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በተለይም ጨቋኙና አምባገነኑ የደርግ ስርአት ተገርስሶ፣ ሀገሪቱ በሰላም ፣በዲሞክራሲ፣በኢኮኖሚ ፣በማህበራዊና በሌሎችም ዘርፎች ህዝቦቿ ፍትሀዊ ተቋዳሽ እንዲሆኑ ግንቦት ሀያ መሰረት መጣሉን ተናግረዋል፡፡
በተለይም
ከ23 አመት በፊት 50 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ የነበረው ሀገራዊ ምርት ፣በአሁኑ ጊዜ በአምስት እጥፍ አድጎ ሀገሪቱ
በምግብ ረሷን እንድትችል አድርጓታል ብለዋል፡፡ይህም ሀገሪቱ በድርቅና በርሃብ ትታወቅ የነበረችው ሀገር ድርቅን
የመቋቋም አቅሟ እየዳበረ እንዲሄድ ማድርጉ ትልቅ እምረታ መሆኑን አስምረውበታል፡፡
በአነስተኛና
ጥቃቅን እንዲሁም በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተፈጠረው መነቃቃትም ሀገሪቱን ወደ ኢንዱስተሪ የሚደረገውን ሽግግር መስመር
የሚያሲይዝና በስራ እድል ፈጠራ ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንዳለ አቶ ሀይለማሪያም ተናግረዋል፡፡
ግንቦት 20 የፈጠረው ድሞክራሲያዊ ስርአት ከ90 በላይ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲፈጠሩና 4 ተከከታታይ ሀገራዊ ድሞክራሳዊ ምርጫዎች እንዲከሄድም አስችሏል፡፡
ይሁንጂ ጠቅላይ ሚንስትሩ ግንቦት 20 የፈጠረውን እድል ተጠቅመው በህጋዊ መንገድ በማይንቀሳቀሱ ሀይሎችና የውጭ ሀይሎችን አላማ ለማስፈፀም በሚንቀሳቀሱት ላይ መንግስት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል፡፡
5ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ በድሞክራሲያዊ መስፈርት በስኬት እንዲጠናቀቅ መንግስት አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡
23ኛው አመት የግንቦት ሀያ ድል የፈጠራቸውን በርካታ ስኬቶች በማስቀጠል ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ማማ ለማውጣት ህዝቡ በጋራ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከተለያዩ የከተመዋ አካባቢዎች የመጡ የበአሉ ተካፋዮች ለኢሬቴድ በሰጡት አስተያየት ግንቦት ሀያ ለብሄር ብሄረሰቦች፣ለሀይማኖትና ለፆታ እኩልነት በር የከፈተ በመሆኑ ትልቅ ቦታ ይሰጡታል፡፡

0 comments:
Post a Comment